ኢዘዲን ካሚል በቴክኖሎጂው ዘርፍ የኢትዮጵያ አምባሳደር እንዲሆን በአፍሪካን ኢኖቬሽን ዊክ ተመረጠ
Your browser doesn’t support HTML5
የ12 ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ የሆነው ኢዘዲን 34 የቴክኖሎጂ የፈጠራ ስራዎችን አበርክቷል፡፡ ከእነዚህ ውስጥም በጸሃይ ሃይል በመጠቀም ከ60 ኪሎሜትር በላይ መጓዝ የሚችል ባለ3 እግር ተሽከርካሪ፣ ከሩቅ በመሆን ሌባን መቆጣጠሪያ፣ እንዲሁም ከንክኪ ውጪ ፈሳሽ ሳሙና የሚረጭ መሳሪያ እና በእጃችን ፊታችንን እንዳንነካ የሚያስታውስ የእጅ ብራስሌት/ጌጥ ሰርቷል፡፡ አፍሪካን ኢኖቬሽን ዊክ ይህን ወጣት የኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ አምባሳደር ይሆን ዘንድ መርጦታል፡፡