የዐይን ብሌናቸውን የሚለግሱ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር ለምን አነስተኛ ሆነ?

.

የኢትዮጵያ የዐይን ባንክ በ17 ዓመት የስራ ዘመኑ የዐይን ብርሃናቸውን የመለሰላቸው ሰዎች 3ሺ አይሞሉም።ከሀገሪቱ ህዝብ ጋር ሲነጻጸር ከህልፈታቸው በኃላ የዐይን ብሌናቸው ለባንኩ እንዲሰጥ የሚፈቅዱት ቁጥር በእጅጉ አነሳ ነው። ይሄን ለመቀየር በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኘው ባንኩ የ2012 ዓመተምህረት የመጨረሻ ቀናትን ከዐይን ብሌን ልገሳ ጋር በተያያዘ ህዝብን ለማንቂያነት እየተጠቀመ ይገኛል። ፖለቲከኞች እና ታዋቂ የኪነጥበብ ሰዎችም እያገዙት ነው።

ባንኩ ከሰሞኑ ሌላም መልካም ዜና ሰምቷል።ፒ3 ለተሰኘነው የተጽዕኖ ፈጣሪዎች ሽልማት የመጨረሻዎቹ ዕጩዎች መካከል አንዱ ሆኗል። ይህ ሽልማት የማህበረሰብ ህይወትን ለማሻሻል ከሚጥሩ ተቋማት መካካል ተለይተው የሚሸለሙበት ሲሆን፣ የኒቨርሰቲ አፍ ቨርጂኒያ እና ኮንኮርዲያ የተሰኙት የትምህርት ተቋማት ከአሜሪካ መንግስት የውጭ ጉዳይ መስሪያቤት ዓለማቀፍ ትብብር ጋር በመቀናጀት የሚያዘጋጁት ነው።

በተያያዥ ጉዳዮች ላይ ከሀብታሙ ስዩም ጋር ቆይታ ያደረጉት የኢትዮጵያ ዐይን ባንክ የግንዛቤ ማስጨበጥ አስተባባሪ አቶ ነጋ ደምሴ -የባንኩን አመሰራረት እና ተግባራት ለአድማቾቻችን በማስታወስ ይጀምራሉ።

Your browser doesn’t support HTML5

የዐይን ብሌናቻውን የሚለግሱ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር ለምን አነስተኛ ሆነ?