"ወደ ውድድሮች የገባሁት ለስራ ማስኬጃ ገንዘብ ስላስፈለገኝ ነው" የፈጠራ ባለሞያ ቃለዳዊት

Your browser doesn’t support HTML5

ቃለዳዊት እስመለዓለም በባህርዳር ከተማ የሚኖር ወጣት የኮምፒውተር ሳይንስ መምህር እና የፈጠራ ባለሞያ ነው፡፡ ከቃለዳዊት ፈጠራ ስራዎች መሃከል በዋናነት የሚነሱት የዶሮ እንቁላል ማስፈልፈያ ኢንኩቤተር፤ የትራፊክ መብራት እና ሙሉ ለሙሉ በሃገር ውስጥ የተመረተ የጸሃይ ሃይል መሰብስቢያ ሶላር ናቸው፡፡ ቃለዳዊት በተለያዩ ውድድሮች ላይ በመሳተፍ ሽልማቶችን አግኝቷል፡፡ በውድድሮቹ ላይ የሚሳተፈውም ያለበትን የበጀት እጥረት ለሟሟላት እንደሆነ ይናገራል፡፡