በ2012 ዓ.ም በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ የተከሰቱ የተማሪዎችን ግጭት የብሔር መልክ ለማስያዝ ማህበራዊ ሚዲያው ሰፊ ሚና ተጫውቷል- ጥናት
Your browser doesn’t support HTML5
የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል በዛሬው ዕለት፤ በ 2012 ዓ.ም ከመስከረም እስከ የካቲት ወር ድረስ በከፍተኛ ትምህርት ማዕከላት ውስጥ የተፈጠሩትን ግጭቶች በተመለከተ 54 ገጽ ያለው ጥናት ይፋ አድርጓል፡፡ በዚህም መስረት ጥናቱ ባተኮረባቸው 6 ወራት ውስጥ ብቻ የ12 ተማሪዎች ሕይወት ማለፉን፣ 57 ተማሪዎች ከባድ እና ቀላል እንደደረሰባቸው እና የትምህርት መስተጓጎል መፈጠሩ ተገልጿል፡፡