ጋቢና መዝናኛ | ቆይታ ከድምጻዊት ሙኒት መስፍን ጋር

Your browser doesn’t support HTML5

ሙኒት መስፍን የሶስት ዘመን ኢትዮጵያዊን ጆሯቸውን ከሚሰጧቸው ባለ ልዩ ቃና ሙዚቀኞች መካከል አንዷ ናት ። “ኖሮ ኖሮ “ የሚለውን ሙዚቃዋን በመሰሉ ብርታትን ቀስቃሽ ሙዚቃዎቿ በወጣቶች ዘንድ ንቃትን ፈጥራለች። የኮ/ል ለማ ደምሰውን “ አስታውሳለሁ” ፣የሰይፉ ዮሃንስን “ የከረሞ ሰው” እና የመሳሰሉትን ዳግም ባቀነቀነችነት አፍታ የአረጋዊያንን ትዝታ ቀሰቅሳለች።ህጻናትን እና ህጻንነትን በሚዘክሩ ስረወቿ ደግሞ ከመጪውን ትውልድ ጋር ተዋወቃለች።