የኮሮናቫይረስ ስርጭት በሲዳማ ክልል እየጨመረ ነው ተባለ
Your browser doesn’t support HTML5
የኮሮናቫይረስ ሥርጭት በሲዳማ ክልል ኮሮናቫይረስ በከፍተኛ ሁኔታ እየተሠራጨ መሆኑን የክልሉ የኅብረተሠብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል። ምክንያቱ የቫይረሱን መዛመት ለመከላከል የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ ክልል ተግባራዊ አለመደረጉ እንደሆነ አመልክቷል።በሀዋሳ ኢንድስትሪ ፓርክም ከአንድ መቶ ሰባ በላይ ሠራተኞች ለቫይረሱ መጋለጣቸውን የኢንስቲትዩቱ ዳይሬክተር ዶ/ር ማቴ መንገሻ ገልፀዋል።