በኢንተርኔት መዘጋት ኢትዮጵያ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ታጣለች

Your browser doesn’t support HTML5

በኢትዮጵያ ለሁለት ሳምንት ሙሉ ለሙሉ የተቋረጠው የኢንተርኔት አገርልግሎት ሀገሪቱን በቀን ከ 4 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ እንደሚያሳጣት 'ኔት ብሎክስ' የተሰኘ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት አስታውቋል። መንግስት አገልግሎቱን ያቋረጠው ሁከትና ብጥብጥ እንዳይባባስ፣ ብሎም የሰዎችን ሕይወትና ንብረት ከጥቃት ለመጠበቅ መሆኑን ቢገልፅም፣ መንግስትን ጨምሮ በኢንተርኔት ግንኙነት ላይ ጥገኛ ሆነው የሚሰሩ የንግድ ተቋማት ለከፍተኛ ክስረት መዳረጋቸውን አስረድተዋል።