“በአርሲና ባሌ ዞኖች ደረሱ ስለሚባሉት ግድያዎች እያጣራን ነው” - ሂዩማን ራይትስ ወች
Your browser doesn’t support HTML5
በአንድ አገር ውስጥ በየትኛውም መልክ ከሚፈፀም የሰብዓዊ መብት ጥሰት መከላከል የመንግስት ኃላፊነት መሆኑን የሂውማን ራይትስ ወች የአፍሪካ ቀንድ ዳይሬክተር ላቲሺያ ባይደር ተናገሩ። የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን መገደል ተከትሎ ኦሮሚያ ውስጥ ኦሮሞ ባልሆኑ ግለሰቦች ላይ ደርሰዋል የተባሉትን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እና ጥቃቶች እያጣሩ መሆናቸውንም ገልፀዋል። የኢንተርኔት መዘጋት ሥራቸውን አስቸጋሪ እንዳደረገባቸውም ተናግረዋል።