"ከፍተኛ ግጭት በነበረባቸው ከተሞች ላይ የምንወስደውን የኮቪድ 19 የናሙና ምርመራ ቁጥር ልንጨምር ነው" ዶ/ር ተገኔ ረጋሳ
Your browser doesn’t support HTML5
ከሃጫሉ ሁንዴሳ ህልፈት በኋላ በነበረው ከፍተኛ የሆን ግጭት እና የተቃውሞ ስልፍ ሳቢያ በመጪዎቹ ሳምንታት ውስጥ የኮቪድ 19 ተጠቂዎች ቁጥር የጨምራል ተብሎ እንደሚጠበቅ የጤና ሚኒስተር አስታወቀ፡፡ በነበረው አለመረጋጋት የኮሮና ምርመራው ከግማሽ በላይ ቀንሶ የነበረ መሆኑን ጠቁሞ አሁን የምርመራ ቁጥሩን በተለይም ግጭት በነበረባቸው አካባቢዎች ጨምሮ ለመስራት መወሰኑን አስታውቋል፡፡ የሚኒስተር መ/ቤቱን የኮሚኒኬሽን ሃላፊ ዶ/ር ተገኔ ረጋሳን ኤደን ገረመው አነጋግራቸዋለች፡፡