ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ “ሕይወትና ንብረት ለመጠበቅ የጦር ኃይሉን በሃገር ውስጥ አሠማራለሁ” ማለታቸው ከጦር መሪዎች ተቃውሞ ገጥሞታል

Your browser doesn’t support HTML5

በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ሆኖ የሞተው ጥቁር አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ ጉዳይ በመላ ዩናይትድ ስቴትስ ከተቀጣጠለው ተቃውሞ ጋር በተነሳው ሁከት ምክንያት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ “ሕይወትና ንብረት ለመጠበቅ የጦር ኃይሉን አሠማራለሁ” ማለታቸው ከጦር መሪዎች ተቃውሞ ገጥሞታል። በሌላ በኩል “ለመሞቱ ሰበብ ሆኗል” በተባለው የፖሊስ አባል ዴሪክ ሾቪን ላይ ተመሥርቶ የነበረው ክስ ወደ ሁለተኛ ደረጃ የግድያ ወንጀል ከፍ እንዲል ተደርጓል።