ከ40 በላይ የፎቶግራፍ ባለሞያዎች የጎዳና ተዳዳሪዎችን ለመደገፍ የተሳተፉበት ድረ ገጽ- ፕሪንትስ ፎር ኢትዮጵያ

Your browser doesn’t support HTML5

ከተመሰረተ ሶስት ሳምንታት ያሰቆጠረ ከ40 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን የፎቶግራፍ አርቲስቶች እየተሳተፉበት ያለው 'ፕሪንትስ ፎር ኢትዮጵያ'ገቢውን ሙሉ ለሙሉ ኑሯቸውን በጎዳና ላይ ያደረጉ ችገረኞችን ቢያንስ በቀን አንዴ ለመመገብ ይውላል፡፡ ከመስራቾቹ አንዷ የሆነችውን ገላኔ ዲሳሳ ከአሜርካ ድምጽ ጋር የነበራት ቆየታ በአጭሩ ተሰናድቷል፡፡
'ፕሪንትስ ፎር ኢትዮጵያ'https://bit.ly/2WPStIB የከ40 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን የፎቶግራፍ አርቲስቶች እየተሳተፉበት ያለ የፎቶግራፍ ድረ፟ ገጽ ነው፡፡ ይህ ድረ ገጽ በዋናነት የጎዳና ተዳዳሪዎችን ለመርዳት ያለመ ነው፡፡

ከዚህ ደረገጽ መስራቾች አንዷ የሆነችው ገላኔ ዲሳሳ ተምሳሌት ኪችን ከተሰኘው እና የጎዳና ተዳዳሪዎችን እየመገበ ያለውን ሬስቶራንት ስራዎች በፎቶግራፍ ለመዘገብ በሄደችበት ጊዜ ያየችው ችግር ሲያሳስባት በኒውዮርክ ከምትኖረው ከባልደረባዋ እድላዊት ሁሴን ጋር በመማከር'ፕሪንትስ ፎር ኢትዮጵያ'የተሰኝ የፎቶግራፍ ድረ ገጽ በመፍጠር ፎቶግራፎችን ገቢ ማሰባሰብ እንደጀምሩ ትናገራለች፡፡

ይህ ድረ ገጽ ገቢ ከማሰባሰቡ ጎን ለጎን ኢትዮጵያውያን የፎቶግራፍ ባለሞያዎችን ብቻ የሚያሳተፍ ሲሆን ይህም የሆነው ደግሞ ኢትዮጵያውያን አርቲስቶችን ለማበረታታተ እና ኢትዮጵያንም በኢትዮጵያውያን ዓይን ለማሳየት መሆኑን ገላኔ ከአሜሪካ ድምጽ ጋር በነበራት ቆይታ ተጨዋውታለች፡፡