ስለ "ደጋፊ " አውታር፦ ምጥን ቆይታ ከቢኒያም ነገሱ ጋር

Your browser doesn’t support HTML5

በመላው ዓለም ላይ በሚታወቁት "ጎ ፋንድ ሚ" ፣ "ኪክ ስታርተር "እና ሌሎች የድጋፍ ማሰባሰቢያ አውታሮች በኩል በየቀኑ በሚሊየን ዶላሮች የሚቆጠር ገንዘብ ይሰባሰባል። የተሰባሰበው ገንዘብ ለተገቢው ዓለማ እንዲውል በማድረግ -የብዙሃንህይወት እንዲቃናም መልካም ተሞክሮ ሆኗል። ያን ተሞክሮ ወደ ኢትዮጵያም ለማምጣት የወሰነ የሚመስለው ቢቲ ቴክኖሎጂስ የተሰኘ ተቋም ደጋፊ የሚሰኝ በሀገራዊ ቋንቋዎች የተሰራ ድጋፍ አሰባሳቢ አውታር ከሰሞኑ ስራ ጀምሯል።