ኢትዮጵያዊው የፎቶ ጋዜጠኛ ሙሉጌታ አየነ የአመቱ ምርጥ ፕሬስ ፎቶ አሸናፊ ሆነ

Your browser doesn’t support HTML5

በኢትዮጵያ የአሶሼትድ ፕሬስ የፎቶ ባለሞያ የሆነው ኢትዮጵያዊው የፎቶ ጋዜጠኛ ሙሉጌታ አየነ እጩ ከሆነባቸው ሦስት ዓለም አቀፍ ሽልማቶች ውስጥ በዋና ዜና ታሪክ ስብስብ አሸናፊ ሆነ። የፎቶ ባለሞያው ያሸነፈበት ስራው ቢሾፍቱ አቅራቢያ በወደቀው ቦይንግ 737 ማክስ 8 አይሮፕላን አደጋ የሞቱ ቤተሰቦቻቸውን አስክሬን ባለማግኘታቸው አውሮፕላኑ የወደቀበት ቦታ ሄደው ፊታቸው ላይ አፈር እየበተኑ ሲያለቅሱ በሚያሳይ አሳዘኝ ፎቶ ነው። ስመኝሽ የቆየ ዝርዝር አላት።