«ከአቅም በላይ የሆነ የለይቶ ማቆያ ሆቴል ወጭ ተጠየቅን» - ኢትዮጵያዊያን መንገደኞች

መንገደኞች በረራ ከመጀመሩ በፊት እንድንፈርም ቀረበልን ያሉትን ቅጽ አጋርተውናል።

ወደ ሀገራችን ለመመለስ ያደረግነው ጥረት ከሀቅም በላይ የሆነ ክፍያ በመጠየቃችን እየተስተጓጎለ ነው ሲሉ በቱርክ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ለአሜሪካ ድምጽ ቅሬታ አቀረቡ።

ሰኞ ዕለት የነበራቸው በረራ ፣«ለለይቶ ማቆያ የሆቴል ወጪ የሚሆን 1750 ዶላር ካልከፈላችሁ» በሚል ተሰርዞብናል ያሉት ቅሬታ አቅራቢዎች ፤ኢትዮጵያ ወደ ግዛቷ የሚገቡ መንገደኞች ለ14 ቀናት ተለይተው እንዲቀመጡ ያስተላለፈችውን ደንብ እንደሚደግፉት ገልጸው፣ ከቲኬት ዋጋ በተጨማሪ እንዲከፍሉ እየተጠየቁት ያሉት ገንዘብ ግን ምክንያታዊነት እንዳነሰው እና በእጅጉ እንዳሳዘናቸው አውስተዋል።

ሀብታሙ ስዩም ዝርዝር አለው።

Your browser doesn’t support HTML5

ከሀቅም በላይ የሆነ «የለይቶ ማቆያ ሆቴል ወጪ» ተጠየቅን ሲሉ ኢትዮጵያዊያን መንገደኞች ቅሬታ አሰሙ