የእርቀ ሰላም ኮሚሽን በደቡብ ክልል ምክክር ጀመረ

Your browser doesn’t support HTML5

የእርቀ ሰላም ኮሚሽን በደቡብ ክልል በሚያከናውነው ሰላምና እርቅ ሥራ ዙርያ ከክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ጋር ዛሬ በጽ/ቤታቸው መከሩ።ኮሚሽኑ በዚህ ወቅት እንዳለው በሕዝብ መካከል ሳይታወቅ የገነገነውን በቀል ቁርሾና ጥላቻዎችን በጥናትና በአገር በቀል እውቀት ላይ ተመስርቶ ለመፍታት የሚያስችል ስራ እየሠራ መሆኑን አስታውቋል።