ሰራዬን ስለምወደው ሁሌም ጠዋት ደስተኛ ነኝ - አንድነት አማረ

Your browser doesn’t support HTML5

በዘንድሮ የዓመቱ በጎ ሰው እጩ እና ልዩ ተሽላሚም ናት፡፡ አንድነት አማረ ትባላለች የኢትዮጲስ የሕፃናት ፐሮግራም መስራች እና አዘጋጅም ናት፡፡ ከጋቢና ቪኦኤ ጋር ቆይታ አድርጋለች፡፡ ኤደን ገረመው ቆይታቸውን እንዲ አዘጋጅታዋለች፡፡
የኢትዮጵስ የሕፃናት ፕሮግራምን መስራት ከጀመረች ወድ 9 ዓመታት አስቆጥረች፡፡ ክ8-12 ዓመት ላሉ ሕፃናት ታሰቦ የሚሰራው ይህ ፕሮግራም ከታቅደለት የእድሜ ክልል ውጪ ባሉ ሕፃናትም ዘንድ በጉጉት ይታያል፡፡ ብዙ ተወዳዳሪ የሕፃናት ፕሮግራሞች በሌሉበት አገር ላይ እየጣረች በምሆኗ የአመቱ በጎ ሰው ሽልማት እጩ እና ልዩ ተሸላሚ ናት፡፡

የኢትዮጵያ ልጆች ተዘንግተዋል ትኩረትን ይሻሉ ስትል የምታሳስበው ጋዜጠኛ እና የሕፃናት ፕሮግራም አዘጋጅ አንድነት አማረ ናት፡፡ አንዴ የተጣመመን ችግኝ ካደገ ለማስተካከል አይቻልም- ይሰበራል ስለዚም ለልጆቻችን ጊዜ ሰጥተን ልንሰማቸው ይገባል፡፡ ለጆቻችንን ዝም በል/በይ ከማለታችን በፊት እንስማቸው ጊዜ እንስጣቸው ትላለች፡፡ ታላቅን ስለማክበር፣ ሃሳብን በስርዓት ስለመግለፅ፣ የሌላውን ነገር ስለማክበር እና ስለ ገንዘብ አያያዝ ማስተማር ይኖርብናል፡፡ አለበልዛ ግን አገር ተረካቢ የሚባል እና ተወዳዳሪ ትውልድ አይኖርም ለዚህም ቤተሰብ፣ መመህራን እንዲሁም የመንግስት አካላት ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ ትመክራለች፡፡