የተማረች ሴት አገር ትመራለች

Your browser doesn’t support HTML5

ሴቶች በጋቢና :- እ.ኤ. አ 2018 ዩኒሴፍ ባውጣው ሪፖርት መሰረት ኢትዮጵያ ወስጥ ከ10 ሴት ልጆች አራቱ ከ18 ዓመት እድሜ በታች ሆነው ወደ ትዳር ይገባሉ፡፡ በተለይም ደግሞ በገጠሪቱ ኢትዮጵያ የሚገኙ ወጣት ሴት ልጆች የዚህ ችግር ሰለባ ናቸው ይሄንንም ሽሽት ብዙዎች ወደ ከተሞች ይፈልሳሉ፡፡
ይሁን እንጂ በከተማም የሚግጥማቸው ችግር የባሰ ከባድ ነው፡፡ በከተሞች ከባድ ለሆነ የጉልበት ብዝበዛ፣ አካላዊ እና ጾታዊ ጥቃት ይጋለጣሉ፡፡ በሳምንት ከ60 ሰዓት በላይ በጉልበት ስራላይ በሚያሳልፉበት በቤት ሰራተኝነት ለመቀጠር ነው የሚገደዱት፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩትም ለዚሁ እረፍት አልባ ስራ በአማካኝ 600 ብር ብቻ ነው የሚከፈላቸው፡፡ ይህም ብቻ አይደለም እነዚሁ ሴቶች የመማር ዕድልም ሆነ፤ ምንም ዓይነት የሕይወት ክህሎት ሳይኖራችው ያድጋሉ፡፡ ይሁንና ይሄንን ችግራቸውን የሚያዋዩት ሰውም ሆነ መንገድ የላቸውም፡፡ ፖፑሌሽን ካውንስል የተሰኘ የጥናት ድርጅት ይሄንን ችግር ለመቅረፍ ለቤት ስራተኞች እና ጎዳና ላይ ለሚኖሩ ሴቶች ማንበበ እና መፃፍ፣ ንፅህና አጠባበቅ፣ ፆታዊ ጥቃትን ለሕግ ስለማድረስ ብሩህ ተስፋ የተሰኘ ፕሮግራም መስርቶ እያስተማረ ይገኛል፡፡ የአገልግሎቱ ተጥቃሚ የሆነችው አንቺ ነሽ ንብረት ስላሳለፈችው ሕይወት ከምታብራራበት ይጀምራል፡፡

ኤደን ገረመው ::