የቤት ለቤት ህክምና -ቀለል ላለ ሕይወት
Your browser doesn’t support HTML5
ነብያት ደመቀ ትባላለች በጤናው ዘርፍ ላይ ያለ አንድ ክፍተት ለመሙላት በሙያዋ እየሰራች ትገኛለች፡፡ የርሆቦት የቤት ለቤት የጤና እንክብካቤ አገልግሎት ድርጅት መስራች እና ስራ አስኪያጅ ናት፡፡ ድርጅቷ ለአረጋዊያን፣ ለፅኑ ህሙማን እና እንክብካቤ ለሚያሻቸው ህሙማን የቤት ውስጥ በባለሞያ የታገዘ ድጋፍ ያደርጋል፡፡ ስለድርጅቱ አመሰራረት እና ስለአገልግሎቱ ከኤደን ገረመው ጋር አጭር ቆይታ አድርጋለች፡፡