ንባብ ለትውልድ

Your browser doesn’t support HTML5

ንባብ ትውልድን ያድናል ብላ በገጠር ለሚግኙ ሕፃናት ስድስት የተረት ምፅሃፍትን ፅፋ በነፃ አከፋፍላለች፡፡ የወርቅውሃ ሃይሌ
'የገጠር ኢትዮጵያ አንብቡ’ መርሃ-ግብር መስራች እና የወርቅውሃ ሃይሌ ፕሮሞሽን ባለቤት ናት፡፡ በገጠር የሚገኙ ሕፃናት ንባብ እንዲለምዱ፣ ስነ-ቃላችውን እና ታሪካቸውን እንዲያውቁ በማለት ከሰላሳ በላይ የሕፃናት መፅሃፍትን ፅፋ፤ ስደስቱን ለህትመት አብቅታለች፡፡ መፅሃፍቶቿም በነፃ ለአንባቢያን ደርሰዋል፡፡

እንኵን የተረት መፅሃፍት ይቅርና መደበኛ የትምህርት መፅሃፍትም አንድ ለአምስት ስለሚሰጡ ሕፃናት የንባብ ባሕል ሳይኖራቸው የማንበብ ክህሎታቸውንም ሳያዳብሩ ያድጋሉ ትላለች፡፡ መፅሃፍትን አግኝተ የሚያንቡትም ቢሆኑ ትርጉም መፅሃፍትን ስለሚያንቡ፤ ብታሪኩ ላይ ከስሙ ጀምሮ ያሉት ነገሮች ለስነ-ልቦናቸው ባዕድ ናቸው የምትለን የወርቅውሃ ሃይሌ ከኤደን ገረመው ተከታዩን ቆይታ አድርጋለች፡፡