ሴትነት እና ዘመናዊ ግብርና

Your browser doesn’t support HTML5

የግብርና ሙያ በኢትዮጵያ ውስጥ ምንም ያልተሰራበት ዘርፍ ነው ትለናለች ኖላዊት ሺመልስ

እንደ ኢትዮጵያ ላሉ እና ግብርና ከሰማኒያ በመቶ በላይ ምጣኔ ሃብታቸው ግብርና ለሆኑ አገራት ዘመናዊ ግብርና ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ነው፡፡ እምብዛም ሴቶች በማይደፍሩት በዚህ ሙያ ወስጥ ወጤታማ ሆና የአገሯን ገበሬዎች እየረዳች እና ሙያውን እያስተዋወቀች ትገኛለች፡፡


ኖላዊት ሺመልስ ትባላለች፡፡ የግብርና ባለሙያ ናት፡፡ የ2017 የማንዴላ ዋሺንግተን ፌሎሺፕ ፕሮግራም አሸናፊ በመሆን ወጣት አፍሪካዊ ተፅእኖ ፈጣሪ ወይም መሪ ወጣቶች መሃከል ሆናለች፡፡ የግብርና ሙያን ለወጣቶች ለማስተዋወቅ በማህበራዊ ድረ-ገፆች ላይ ትፅፋለች፡፡ በአሁን ሰአት በሩዋንዳ እና በኢትዮጵያ እየተንቀሳቅሰች ለግብርና ባለሙያዎች ስልጠና ትሰጣለች፡፡ ከኤደን ገረመው ጋር ቆይታለች፡፡