ከሀዘን ባሻገር ፣ የአምስቱ ሹማምንት መታሰቢያ ምሽት

Your browser doesn’t support HTML5

ፊታቸው በሀዘን የደመነ፣ጥቁር የለበሱ እንግዶች በቅርቡ ከተገደሉት ሹማምንት ፎቶ ግራፎቹ ፊት ለፊት በተቀመጠ የሀዘን መግለጫ መዝገብ ላይ ሀሳባቸውን በየተራ ያሰፍራሉ፡፡ማዘናቸውን፣መከፋታቸውን፣ለመዝገቡ የደበቁት አይመስልም፡፡ መሸትሸት ሲል ፣ሀዘንተኛው ቦታውን ሲይዝ መነጋገሪያውን የጨበጡ ሁሉ ግን ታደሚው ከሀዘንና እና መከፋት ባሻገር ስለ ሀገሩ በእጅጉ ማሰላሰል እንዳለበት ያሳስቡ ነበር፡፡