አንድ ፓርቲ መሆን “የሚታሰብ አይደለም” - ህወሓት

Your browser doesn’t support HTML5

ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚስተዋለው የሰላም እጦትና አለመረጋጋት ተጠያቂው የኢህአዴግ አመራር ነው ሲል የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አስታውቋል። ማዕከላዊ ኮሚቴው መቀሌ ላይ ለአራት ቀናት ያካሄደውን ስብሰባ አስመልክቶ ትናንት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ “የግንባሩ አመራር ከፓርቲው እምነትና ፕሮግራም ውጭ እየሄደ ነውም” ብሏል ። “ኢህአዴግ ውሁድ ፓርቲ ሊሆን ነው” ስለሚባለውም ኮሚቴው ሲናገር “የግንባሩ አባል ድርጅቶች በተለያየ አቅጣጫ እየተጓዙ ባሉበት ጊዜ የማይታሰብ ነው” ብሏል።