ኢትዮጵያዊያን አሁንም በኬንያ እሥር ቤቶች አሉ

Your browser doesn’t support HTML5

ከ150 በላይ ኢትዮጵያዊያን አሁንም በኬንያ እሥር ቤቶች ውስጥ እንደሚገኙ የኢትዮጵያ ኢምባሲ አስታወቀ። በኢምባሲዉ የቆንሲላ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ቴዎድሮስ ተፈሪ ኢምባሲዉ ትላንት ከታንዛኒያ ወደ ኬንያ የተባረሩ 54 ኢትዮጵያዊያንን ወደ ሀገር ማስመለሱንም አክለዉ ገልጸዋል።