የሱሉልታ ከተማ ነዋሪዎች አቤቱታ
Your browser doesn’t support HTML5
በሱሉልታ ከተማ ቤት ሠርተው የሚኖሩ የከተማ አስተዳደሩ ቤታቸው በአንድ ሣምንት ውስጥ እንደሚፈርስ አስጠንቅቆ ይፈርሳሉ ያላቸው ቤቶች ላይ የቀለም ምልክት ማድረጉን ገለፁ። የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በበኩሉ ሥራው ህግን የማስከበር በመሆኑ ህጋዊ ሠነድ እና ማስረጃ ያላቸው ባለ ይዞታ ማስረጃቸውን ማቅረብ ይችላሉ ብሏል።