አለማ ካውዳይስ የመኖ ማቀነባበሪያ ሠራተኞቹን ከሥራ አገደ

Your browser doesn’t support HTML5

ቢሾፍቱ የሚገኘው አለማ ካውዳይስ የመኖ ማቀነባበሪያ የለምንም ምክንያት ከሦስት መቶ በላይ ሠራተኞች ከሥራ ማገዱን የድርጅቱ ሠራተኞች ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ። የከተማው ሠራተኛ እና ማኅበራዊ ዋስትና ጽሕፈት ቤት በበኩሉ ድርጅቱ ህግ አክብሮ እንዲሰራ ብዙ ግዜ ቢነግረው ሊታረም አልቻለም ይላል።