የአሜሪካ መንግሥት መዘጋት ምንድነው? ለምን?

Your browser doesn’t support HTML5

በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕና በተወካዮች ምክር ቤቱ አፈጉባዔ ናንሲ ፔለሲ መካከል የተፈጠረው መፋጠጥ ለውጥ አላሳየም። መንግሥቱ ከወር በላይ የተዘጋው በዚሁ ሰበብ ነው። እንደገና ላለመዘጋቱ ዋስትና የለም። “ከፕሬዚዳንቱ ዛቻና ፉከራ በመነሣት ቢዘጋ አይደንቀኝም” ይላሉ የኦሃዮ ዩኒቨርሲቲው የፖለቲካ ሣይንስ ፕሮፌሰር ዶ/ር ብሩክ ኃይሉ።