በምዕራብ ጎጃም ዕጩ ሁለት ዶክተሮች ተደብድበው ተገደሉ

Your browser doesn’t support HTML5

ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለዶክትሬት ማጠናቀቂያ ጥናታቸው ወደ ምዕራብ ጎጃም ዞን ጎንጅ ቆለላ ወረዳ ወደ አዲስ አለም ከተማ ተጉዘው የነበሩ ግለሰቦች ላይ በተፈፀመ ጥቃት ሁለቱ ሲገደሉ አንዱ መቁሰሉን የዞኑ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ።