በቡራዩና አካባቢው የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 58 መሆኑን አምነስቲ አስታወቀ

Your browser doesn’t support HTML5

በቡራዩና አካባቢው የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 58 መሆኑን ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን እስካሁን ከየሆስፒታሉ የተሰበሰበው መረጃ በእጃቸው እንዳልደረሰ ገልጾ ቁጥሩ አምነስቲ የጠቀሰው ሊሆን እንደሚችል ተናግረዋል።