ኤስፒኤልኤም-አይኦ የኪርን ዘመን መራዘም አወገዘ

Your browser doesn’t support HTML5

የደቡብ ሱዳኑን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪርን የሥልጣን ዘመን በሦስት ተጨማሪ ዓመታት ለማራዘም የሃገሪቱ ፓርላማ ያሳለፈውን ውሣኔ በብርቱ እንደሚያወግዝ በሪክ ማቻር የሚመራው “የሱዳን ሕዝብ ነፃ አውጭ ንቅናቄ - በተቃውሞ” የሚባለው ቡድን አሳውቋል።