ከኦሮሚያ የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች የመፈናቀል ምክኒያት

Your browser doesn’t support HTML5

ከኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን የተፈናቀሉት ነዋሪዎች የመፈናቀላቸው ምክኒያት “ፍርሃት እንጂ የፀጥታ ችግር አይደለም” ሲሉ የዞኑ የሰዲ ጨንቃ ወረዳ አስተዳዳሪ ገለፁ።ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች በበኩላቸው፤ “የተደራጁ ኃይሎች ንብረት አቃጥለው፣ መሰረታዊ አገልግሎት እንዳናገኝ ከልክለው፣ ወደ ሀገራችሁ ሂዱ ብለው ሲያባርሩን ነው የኖርንበትንና ንብረት ያፈራንበትን መንደር ጥለን የተሰደድነው።” ይላሉ።