በዋሽንግቶን ዲሲና አካባቢዋ አዳጊ ልጆችን ከመጠለፍ ማዳን

Your browser doesn’t support HTML5

ሴትና ወንድ አዳጊ ልጆችን አፍኖ በመጥለፍ አሳልፎ በገንዘብ የመግዛትና የመሸጥ ወንጀል በዩናይትድ ስቴትስ በእጅጉ በመበራከት ላይ ይገኛል። ሀገር አቀፍ የህገወጥ የፆታ ንግድን የሚከታተለው ድርጅት በዘረጋው የስልክ መስመር ቢያንስ 20 አዳዲስ መረጃዎችን በየቀኑ ይመዘግባል። ሜሪላንድ ግዛት የሚገኘው የምርመራ ፖሊስ አፋኞቹና ህገወጥ ድርጊት ፈፃሚዎቹን ለመያዝ ከመስራት ይልቅ አዳጊ ልጆቹን የማዳን ስራ ላይ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ላይ ይገኛል።