እስረኞችን የመፍታትና ማዕከላዊን የመዝጋት ውሳኔው በአስቸኳይ ግልጽ እንዲደረግ ተጠይቋል

Your browser doesn’t support HTML5

የኢትዮጵያ መንግሥት ለዘመናት ሲክደው የነበረውን የፖለቲካ እስረኞች አምኖ ለመፍታት መወሰኑ የሚያስደስት ነው ያሉ ከዚህ ቀደም ታስረው የተፈቱ ሦስት የኢንተርኔት አምደኞች፤ “ነገር ግን ጉዳዩ እንደተለመደው የፖለቲካ ማታለያ ሆኖ እንዳይቀር ውሳኔው ግልጽ ሊደረግና በሀገሪቱ ውስጥ ባሉ እስር ቤቶች በየትኛውም የፖለቲካ አመለካከታቸው የታሰሩ ሰዎች በአስቸኳይ ሊፈቱ” ይገባል ብለዋል።