“ጠቅላይ ሚኒስትሩ ካላነጋገሩን ወደ ሥራ አንገባም ብለናል” ወ/ሮ ነኢማ አሕመድ የፓርላማ አባል

Your browser doesn’t support HTML5

ኢትዮጵያ ውስጥ እየተከሰቱ ላሉ ግጭቶች፣ሞቶችና ንብረት መውደምን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ቀርበው ማብራሪያ ሊሰጡን ይገባል ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጥያቄ ማቅረባቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ። ለጥያቄዎችቻቸው ቀርበው ምላሽ ካልሰጧቸው ሥራቸውን መቀጠል እንደሚሳናቸው መናገራቸውን ጠቁመዋል።