በሳዑዲ ያለፈቃድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በፖሊሶች እየተያዙ ነው

Your browser doesn’t support HTML5

ያለመኖሪያና ስራ ፈቃድ በሃገሪቱ የሚኖሩ ህገወጥ ስደተኞችን እንዲወጡ የሚያዘውን የቀነ ጊዜ ገደብ በተደጋጋሚ ሲራዘም ቆይቷል። ከቀናቶች በፊት የሳውዲ መንግስት በሃገሪቱ የተገኙትን ህገወጥ የሚላቸውን ሁሉ በማሰር ላይ ይገኛል። በሪያድ የማህበረሰብ መሪ የሆኑት አቶ ሻውል ጌታሁን "ኢትዮጵያውያኑን ለመርዳት የምንችልበት ጊዜ ላይ አይደለንም" በማለት ገልፀውልናል። በሳዑዲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ማምሻውን ጥቂቶቹን ጠይቀን ነበር።