ዘረኛነትና ፀረ-ዘረኛነት በሻርለትስቪል-ቨርጂንያ
Your browser doesn’t support HTML5
ዩናይትድ ስቴትስ የቨርጂንያዪቱ ሻርለትስቪል ከተማ ውስጥ ባለፈው ቅዳሜ የተነሣውን የሕይወት መጥፋት ያስከተለ ሁከት የጫሩትን ኔኦ ናዚዎችና የነጭ የበላይነት አስተሳሰብ አራማጅ የሆኑትን ኩ ክለክስ ክላን የሚባል ቡድን አባላት “ወንጀለኞችና ወንበዴዎች” ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ አውግዘዋቸዋል።