ገዢው ኢሕአዲግ እና 16 ተቃዋሚ ፓርቲዎች የአገር ውስጥና የውጭ አገር ታዛቢዎች በተገኙበት በድርድር አጀንዳዎች ላይ መነጋገር ጀምረዋል
Your browser doesn’t support HTML5
የቅድመ ድርድሩ ከተጀመረ ወዲህ ታዛቢዎች ሲገኙ የዛሬው ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ገዥው ፓርቲ ኢሕአዲግ ለድርድር ፍቃደኛ የሆነባቸውና እንደዚሁም የማይቀበላቸው ርዕሶች ዛሬ ይፋ መደረግ ጀምረዋል። በምርጫ ሕጉ ላይ ለመነጋገር መፍቀዱ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ ግን መነጋገር እንደማይቻል ማመልከቱ ከሚጠቀሱት መካከል ናቸው።