በዮናታን ላይ የተላለፈው ውሳኔ የመናገር ነፃነትን የሚፃረርና “አሳፋሪ” ነው ሲል አምነስቲ ገለፀ
Your browser doesn’t support HTML5
በእስር ላይ የሚገኘው የቀድሞው የሰማያዊው ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ላይ ሽብርተኝነትን በማበረታታት በሚል በቀረበበት ክስ የተላለፈው የጥፋተኝነት ውሳኔ ሐሳብን የመግለፅና እና በፌስቡክ ፁሑፎችን የማውጣት መብት የሚፃረር “አሳፋሪ” ውሳኔ ነው ሲል ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ገለፀ።