ሀዲስ ዓለማየሁ የናስ ኃውልት ቆመላቸው
Your browser doesn’t support HTML5
ደራሲ፣ ዲፕሎማት፣ አርበኛ፣ መምህር ሀዲስ ዓለማየሁ ከነኀስ የተሠራ ኃውልት ቆመላቸው፡፡ ለሀዲስ ዓለማየሁ ደብረ ማርቆስ ከተማ ላይ የቆመውን ከነኀስ የተቀረፀ ኃውልት መርቀው የገለጡት የባሕልና ቱሪዝም ሚኒስትር ሂሩት ወልደማርያም ናቸው፡፡ ዛሬ በተከናወነው ሥነ-ሥርዓት ላይ የክብር ዶክተር ሀዲስ ዓለማየሁ በሕይወት ሳሉ ያላሣተሟቸው ግጥሞቻቸውን የያዘ መድብል ታትሞ ይፋ ተደርጓል፡፡