ቅዳሜ ምሽት በባህር ዳር የደረሠ ፍንዳታ የሠው ሕይወት አጠፋ

Your browser doesn’t support HTML5

ከትናንት በስቲያ ቅዳሜ ምሽት በባህር ዳር መስቀል አደባባይ በሚገኘው ሚሊኒዬም የወጣቶች ስፖርት ማዕከል ውስጥ ፍንዳታ ደርሶ የሁለት ሰው ሕይወት ማጥፋቱን ቢያንስ አምስት ሠዎች መቁሰላቸውን ከአካባቢው ያነጋገርናቸው ምንጮች ገልፀውታል፡፡