የኢትዮጵያ ጦር ኤል ቡርን ለቅቆ ወጣ

  • ቪኦኤ ዜና

Your browser doesn’t support HTML5

ማዕከላዊ ሶማሊያ ውስጥ ቁልፍ የሚባል ወታደራዊ መደብ ይዞ የቆየው የኢትዮጵያ ጦር ያለአንዳች የቅድሚያ ማስታወሻ አካባቢውን ጥሎ መውጣቱን የኤል ቡር ከተማ ነዋሪዎችና የከተማዪቱ አስተዳዳሪ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡ የኢትዮጵያ ጦር ኤል ቡርን ለቅቆ መውጣትን ተከትሎ በከባድ የታጠቁ የአማፂው ቡድን አል ሻባብ ተዋጊዎች ያለ አንዳች መሰናክል ዛሬ ማለዳ ላይ ከተማዪቱን መቆጣጠራቸው ተነግሯል፡፡