የእሰጥ-አገባ ክርክር:- ኢትዮጵያ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥና ቀጣይ አቅጣጫዎች

የኢትዮጵያ ካርታ

“የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ባይታወጅ ኖሮ የት ነው የሚቆመው አመጹ? የት ነው ጋብ የሚለው ነገር በጣም አጠያያቂ ነው የነበረው።” አቶ አታክልት አምባዬ። “የአስቸኳይ ጊዜውን አዋጁን ያወጁትም ሰዎች መፍትሔው እንፈልጋለን መፍትሔ አልተፈለገም። መፍትሔው ምንድ ነው? ችግሩ ምንድነው? የሚለው ነገር ላይ ውይይት አላየንም።” አቶ ፈቃደ ሸዋ ቀና።

Your browser doesn’t support HTML5

ድሕረ-አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኢትዮጵያ! .. የክርክሩን የመጀመሪያ ክፍል ከዚህ ያድምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

እሰጥ-አገባ:- ድሕረ-አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኢትዮጵያ! .. ሁለተኛውን ክፍል ከዚህ ያድምጡ።

በወቅታዊ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ያተኮረው ክርክር በአስቸኳይ ጊዜው አዋጅ ወቅት በመንግስት የተወሰዱ እርምጃዎች አንድምታ እና ድሕረ-አስቸኳይ ጊዜ የተለያዩ ቀጣይ ሁኔታዎች ይዳስሳል።

የክርክሩ ተሳታፊዎች፤ አቶ አታክልት አምባዬ፤ የፍኖተ-ሰሜን የአማርኛና የትግርኛ ወርሃዊ መጽሄት አሳታሚና የፍኖተ ትንሳኤ ሚዲያና አሳታሚ ድርጅት ባለቤት፤ ከአዲስ አበባ።

አቶ ፈቃደ ሸዋ ቀና በዩናይትድ ስቴትሱ ብሔራዊ የጤና ምርምር ተቋም በጥናት ሥራ የተሰማሩና በኢትዮጵያ የፖለቲካ ጉዳዮች በመጻፍ የሚታወቁ ናቸው።