"የሰብዓዊ መብት በአፍሪካ አደጋ ላይ ወድቋል"- አምነስቲ ኢንተርናሽናል

Your browser doesn’t support HTML5

ዓለም አለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት በዓለም ደረጃ የሚሰማው መርዛማና ከፋፋይ ልፈፋ እንዲሁም በሰዎች ላይ የሚፈጸሙ የጭቃኔ ተግባሮች የሚያሳዩት ቸልተኝነት ሊያስከትሉ ስለሚችሉት አደጋ ያስጠነቅቃል። አምነስቲ ኢንተርናሽናል የተባለው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅት ስለ አፍሪካ ባወጣው ዘገባ ደግሞ አፍሪካ ውስጥ በሚካሄዱ ግጭቶች፣ በፍጹማዊ አገዛዝ መበራከትና በፖለቲካዊ ውጥረት ምክንያት የሰብአዊ መብት ይዘት አደጋ ላይ መውደቁን አስገንዝቧል።