"በሸዋሮቢት እስር ቤት ከፍተኛ የማሰቃየት ተግባር ተፈጽሞብናል" ተከሳሾች

Your browser doesn’t support HTML5

የሙስሊም ማኅበረሰብ ጥያቄዎች መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ከእስር እንዲፈቱ ተንቀሳቅሳችኋል በሚል በእነከድር መሐመድ መዝገብ በሽብር አድራጎት የተከሰሱ 19 ሰዎች በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤት በነበራቸው ቀጠሮ፤ በሸዋሮቢት እስር ቤት ከፍተኛ የማሰቃየት ተግባር እንደተፈፀመባቸው ለችሎት ማስረዳታቸውን ጠበቃቸውና ቤተሰብ ለአሜሪካ ድምጽ ገለጹ።