“ሞት በኔ አልተጀመረም” ምሩፅ ይፍጠር በህይወት አለ!

Your browser doesn’t support HTML5

ማርሽ ቀያሪ በመባል የሚታወቀው ምሩፅ ይፍጠር በ72 አመቱ ከትላንት በስትያ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል የሚል ዜና ደርሶን እኛም ዜናውን ለናንተ አድርሰናል። ስልኩን በማፈላለግ አግኝተን አነጋግረነዋል። በሳምባ ህመም ምክንያት ከአመት ተኩል በላይ ቢታመምም ህክምናን በመከታተል አሁን በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኝ ነግሮናል።