በጌዲኦ ዞን የ23 ሰው ሕይወት መጥፋቱን የክልሉ መንግሥት አረጋገጠ

Your browser doesn’t support HTML5

በደቡብ ክልል በጌዲኦ ዞን በሦስት ወረዳዎች ባሉ የተለያዩ ከተሞች፤ በዲላ፣ በይርጋ ጨፌ፣በወናጎ፣ በፍስሃገነትና በወረዳዎቹ አካባቢ ባሉ ከተሞች “በተፈጠረ ግጭት ከአካባቢው ተወላጆች በተሰነዘረብን ድንገተኛ ጥቃት ቁጥራቸው ለጊዜው ያልታወቁ ሰዎች ተገደሉ፣ ንብረታችን ተቃጠለ አሁን ቤተክርስቲያ ከተጠለልን አራኛ ቀናችን ነው” ሲሉ ያነጋገርናቸው የአካብባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ።