በኢትዮጵያ ከትናንት ጀምሮ የሚተገበር ለስድስት ወር የሚዘልቅ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ታወጀ

  • እስክንድር ፍሬው

Your browser doesn’t support HTML5

የኢትዮጵያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት፥ በሃገሪቱ ያንዣበበውን አደጋ ለመቀልበስ የስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ማወጁን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ አስታወቁ። በተለመደው ሁኔታ በመቀጠል ያለውን ችግር መፍታት አዳጋች መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል። በመሆኑም የስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ በማወጅ ባጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ሰላምና መረጋጋት መመለስ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ብለዋል።