"ልጅን ያህል ነገር ያለበትን ሳላውቅ እንዴት ዝም ልበል?" የዮናታን ተስፋዬ እናት

Your browser doesn’t support HTML5

ከትላንት በስቲያ ቅዳሜ ከአዲስ አበባ ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኘው የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ላይ በደረሰው የእሳት ቃጠሎ አደጋ የ23 ሰዎች ህይወት ማለፉን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታውቋል። በሌላ በኩል ቂልንጦ ማረሚያ ቤት የሚገኙ የእስረኛ ቤተሰቦች ታሳሪ ቤተሰቦቻቸው የት እንደሚገኙ ማወቅ እንዳልቻሉና ሊጠይቁ በሄዱበት ወቅት እንግልት እየደረሰባቸው እንደሆነ ለአሜሪካ ድምጽ ገልፀዋል።