የአትሌት ፈይሣ ሌሊሣ ቤተሰብ ምን ይላሉ?

Your browser doesn’t support HTML5

በሪዮ ኦሎምፒክ የተሳተፉ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ከትላንት በስቲያ ማክሰኞ ማታ አዲስ አበባ ዓየር ማረፊያ በደረሱበት ወቅት የመንግሥት ባለስልጣናት በተገኙበት ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። በእሁዱ የኦሎምፒክ የወንዶች ማራቶን ውድድር የብር ሜዳሊያ የተቀዳጀው ፈይሳ ሌሊሳ ውድድሩን ሲያጠናቅቅ ያሳየው በኢትዮጵያ የመንግሥት ተቃዋሚዎች የሚዘወትር ምልክት ልዩ ትኩረት መሳቡ ይታወቃል።