“እጁ ረጅም የኾነ ኃላፊነት የማይሰማው መንግሥት ነው” አቶ አበባው አያሌው

Your browser doesn’t support HTML5

የኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምሕርት መግቢያ ፈተና መሰጠት ከማኅበራዊ መገናኛ ድረ ገጾች መዘጋት ጋር መያያዙ እያነጋገረ ነው። አቶ አበባው አያሌው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጥበብና ዲዛይን ት/ቤት የኢትዮጵያ ሥነ ጥበብና ታሪክ መምሕር ናቸው። በልዩ ልዩ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ትንታኔ በመስጠትም ይታወቃሉ። አቶ አበባው በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየት እንዲሰጡ ጽዮን ግርማ አነጋግራቸዋለች።