በሜዲተራንያን ባህር ሲጓዙ የነበሩ 1,262 ዜጎችና ስደተኞች በተደረገላቸው የነብስ አድን እርዳታ በህይወት መትረፋቸው ተገለጸ

Your browser doesn’t support HTML5

ከሊብያ የተነሱት ተጓዦች ግዙፉን ባህር በሰባት ከጎማ በተሰሩና በዓየር የሚሞሉ ጀልባዎች፥ በአንዲት የቁሳቁስ መጫኛ ትንሽ ጀልባና በአንዲት ሌላ አነስተኛ ሰው ለማሳፈሪያነት ያልተሰራች ጀልባ አቋርጠው ወደ ጣሊያን ለማምራት በመጣጣር ላይ ሳሉ ነው የጣሊያንና የአየርላንድ ባህር ኃይሎች ከጣሊያን የባሕር ጠባቂዎች ጋር በመሆን ያዳኗቸው።